ዕድራችን


ከየት ወዴት!

የስው ልጅ ስለነገ ቀጣይ ሕይወቱ በትክክል መተንበይ አይቻለውም። በእያንዳንዱዋ ከጥቂትዋ የጊዜ ክፍልፋይ አፍታ ጀምሮ የእያንዳንዳችን አኗኗር ከፍና ዝቅ ሊቀያየር ሲችል እስከአናካቴው በመኖርና ባለመኖር ያለውም ውሳኔ ከእኛነታችን ወጥቶ ቀድመን ልንጠነቀቅለት የማንችለውና ከመጣ ጊዜ የማይሰጥ የቁርጥ ቀን ሆኖ ይጋፈጠናል። ሆኖም ስለነገ ባናውቅ ነገር ግን ቢሆንስን በማሰብ ብቻ ቢያንስ የሐዘኑን ድርርቦሽ ለመቀነስ ዘዴ መወጠን እንችላለን።

መከበር በቁም ሳሉ በሕይወት ዘመን ብቻ አይደለምና ከወረስነው ፀሎታዊ አባባል «አሟሟቴን አሳምርልኝ!» ያለስቃይ አጠናቀኝ ለማለት ብቻ ሳይሆን አሸኛኘቱንም ጠቅልሎ ነው። በተለይ ከትውልድ ቀዬአችን ከዘመድ አዝማድ በመራቅ ለሰፈርን ያ መምጫው የማይታወቅ ግን ሲመጣ አፍጦ የተጋፈጠን ዕለት «እኔ ከሞትኩ...» ዓይነትም እንዳይመስልብንም ጭምር ቀድሞውኑ ካልተዘጋጀንበት የሕይወታችን ማብቂያ ማሰሪያው የሚቆጭ ሊሆን ይችላል።

የሲድኒ የዕድር መረዳጃ ማኅበር በግንቦት 2010 የተመሰረተውም በእዚሁ የሀሳብ ውጥን በመነሳት ነበር። በሀሳብ ደረጃ በአካባቢዋ በሚኖሩ ነባርና ችግሩን በተግባር ካስተዋሉት በመስራቾቹ መሀል ለረጅም ጊዜ ሲወያዩበት ቆይተዋል። ወደመጨረሻው ላይም የዓንድ ዓይነት አመለካከት ያላቸው ሰዎች መብዛትም የጠቅላላ የነዋሪ ማኅበረሰቡም እየተዋለደም ሆነ አዲስ ነዋሪነት ከመጣው ተጨምሮ የነዋሪው ቁጥር እጅግ እየተበራከተ ከመምጣቱ ተደማምሮ እነዚህ ሰዎች ከብዙ ልፋትና ውጣ ውረድ በኋላ በዕዚህ ዕለት ለዕድሩ ጅማሬ አንድ መሠረት ጣሉ።

በዕለቱ የዕድሩን አስፈላጊነት ከተሰብሳቢ ጋር ተወያይቶና መክሮበት የሚያሻማ ሌላ ሀሳብ ወይም እምብዛም መቋቋሙን የማያምን ባለመገኘቱ ለመነሻ ያህል በተዘጋጀ የሕግ ረቂቅ ላይ ሀሳብ በመለዋወጥ ሥራውን ጀመረ።

ዋና ዓላማውና ተልዕኮው አንድ በእዚህ ዕድር የታቀፈን ሰው ወይም አባል የመምጫው ቀን በማይታወቀው የድንገተኛ የሞት አደጋ በእራሱ ወይም ከቤተሰቡ መሀከል ቢከሰት ከወገናዊነት ወይም ከሰብዓዊነት ሀዘን ተካፋይነት ጥቂት ገፋ ያለ በወቅቱ ፈጦ ለሚመጣው ወጪ የገንዘብ ድጋፍ የሚሰጥ አጋዥ አካል ነው።

ሰብአዊ ተፈጥሮአችን ሆኖ መሽቶ ሲነጋ ተነስቶ ለዕለታዊ እንጀራ መሮጥን እንጂ ይደርስብኛልን ስለማናስብ ወይም የእዚህ ተፈጥሮአዊ ጥሪ የቀጠሮው ቀን ባለመታወቁ በእዚህች በጣፈጠች የምድር ሕይወታችን መሀል የሞት ሀዘን ድንገት ሰርጎ ሲገባ ሀዘኑ ብቻውን አይጋፈጠንም። የእዚህ መረዳጃ ዕድር መመስረት ጠቃሚነቱም በእዚሁ ጭብጥ ላይ ነው። ከሀዘን ተካፋይነቱ ሻገር ብሎ የየግል ገበናችንን አሽሞንምኖ በወቅቱ ከሚያስጨንቀን የሀሳብ ምጥ ይካፈልልናል።

በእዚህ ጉባኤ በተሰበሰቡና በርካታ ቁጥር ባላቸው አባላት የተጀመረ እንቅስቃሴ ዛሬ ዓመታትን ከአስቆጠረ በኋላ በአባለት የድንገተኛ ሀዘን ጊዜ ፈጥኖ በመድረስ እየረዳ ዛሬ ይኸው ጠቅላላ የአባላቱ ቁጥር በሚያበረታታ ሁኔታ ከፍ ብሎ ይገኛል።

መዋቅርCurrently serving as executive committee
July 2019-June 2021
    1. Mr. Kedisew Hunegnaw
        Chairman
    2. Mr. Endeshaw Wegayehu
        Deputy Chairman & Secretary
    3. Mr. Demeke Jembere
        Finance
    4. Mr. Basazinew Yalew
        Public Relation & Media coordinator
    5. Mr. Gedion Delbo
        Logistic